Skip to content Skip to navigation

የኦሮሚያ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ልዑካን ቡድን ከሁለት የኬንያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር የልምድ ልውውጥ አደረገ :: በኦሮሚያ ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ነመራ ቡሊ እና በኦሮሚያ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ገመቹ አራርሳ የተመራው ልዑካን ቡድን ሰኔ 30 ቀን 2013 ዓ.ም. ከኬንያታ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ቻንስለር ፕ/ር ፖውል ወይናይና እና ከዩኒቨርሲቲው የማኔጅመንት አባላት ጋር ተወያይቷል። በተመሳሳይ ልዑካን ቡድኑ ሐምሌ 01 ቀን 2013 ዓ.ም. ከናይሮቢ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ቻንስለር ፕ/ር ስቴፈን ኪያማ እና ከዩኒቨርሲቲው የማኔጅመንት አባላት ጋር ምክክር አድርጓል።

የኦሮሚያ ስቴት ዩኒቨርስቲ ልዑካን ከኬንያታ እና ናይሮቢ ዩኒቨርሲቲዎች የማኔጅመንት አባላት ጋር በዩኒቨርሲቲዎቹ መካከል ጉድኝት በመመስረት በትብብር ለመስራት ተስማምተዋል። ልዑካን ቡድኑ የኬንያታ ዩኒቨርሲቲ ዋና ካምፓስ ፋካልቲዎችንም ጉብኝቷል።

English

የኦሮሚያ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ልዑካን ቡድን ከሁለት የኬንያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር የልምድ ልውውጥ አደረገ